Download Amharic Brochure (PDF, 272KB)
ስላለዎት የአካለ ጉዳተኛ ድጋፍ አገልግሎት በተመለከተ እንዴት ቅሬታ ለማቅረብ እንደሚችሉ።
አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ስለሚቀርብላቸው የአካለ ጉዳተኛ ድጋፍ አገልግሎት ደስተኞች አይደሉም።
በቪክቶሪያ ውስጥ ስለ የአካለ ጉዳተኛ ድጋፍ አገልግሎት በተመለከተ ለሆነ ሰው ማነጋገር ከፈለጉ፤ ለአካለ ጉዳተኛ አገልግሎቶች
ባለስልጣን/Disability Services Commissioner መናገር ይችላሉ። እንዲሁም እኛን ለማነጋገር እንዲረዳዎ የርስዎን
ቤተሰብ ወይም ጓደኞች መጠየቅ ይችላሉ።
ነገሮችን በበለጠ ለማሻሻል ከርስዎ እና ከድጋፍ አቅራቢ አገልግሎት ጋር አብረን እንሰራለን። የምናቀርበው አገልግሎት ያለክፍያ
በነጻ እና በመንግሥትና በሌሎች አገልግሎቶች ላይ ተጽእኖ የሌለበት ሙሉ በሙሉ በራሱ የሚመራ ነው።
አንዳንድ ሰዎች አስተርጓሚ ይፈልጋሉ ስለዚህ እኛን በሚያነጋግሩበት ጊዜ ከእንግሊዝኛ ባሻገር በሌላ ቋንቋ መጠቀም ይችላሉ።
ያለክፍያ በነጻ አስተርጓሚ ማቀናጀት እንችላለን።
እኛን ለማነጋገር: